የዓለም ቀይ መስቀል ለትግራይ ተጨማሪ እርዳታ እንዲደርስ ጥሪ ቀረበ

የዓለም ቀይ መስቀል ለትግራይ ተጨማሪ እርዳታ እንዲደርስ ጥሪ ቀረበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የዓለም ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማህበራት ፌደሬሽን በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በግጭቱ ተጎጂ ለሆኑት ተጨማሪ እርዳታ እንዲደርስ ጥሪ አቀረበ።

የትግራይ ክልል ዋና ከተማን የጎበኙት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ፍራንሴስኮ ሮባ በክልሉ ያለው ነገር በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸው፤ በጦርነቱ ምክንያት በደረሰው ጉዳት ከፍተኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ህጻናት፣ ሴቶች እና አረጋውያን መሆናቸውንም ይፋ አድርገዋል።
ሆስፒታሎች አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው መሰረታዊ የሕክምና መስጫ ቁሳቁሶች እንኳን እንደሌላቸው የጠቆሙት ሓላፊው፤ በተጨማሪነትም የምግብ እጥረት አካባቢውን እንደሚያሰጋውም ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት በርካታ ንጹሀን ዜጎችን ተጋላጭ እንዳደረገና ችግሩ በጎረቤት አገራትም ተጽዕኖ እንደፈጠረ የዓለም ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማኅበራት ፌዴሬሽን ከቀናት በፊት መግለጹ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY