ኢትዮጵያ ውስጥ በወር በነዳጅ ሰበብ 9 ቢሊዮን ብር ይዘዋወራል ተባለ

ኢትዮጵያ ውስጥ በወር በነዳጅ ሰበብ 9 ቢሊዮን ብር ይዘዋወራል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ በነዳጅ ሰበብ የሚገላበጠው ገንዘብ በወር 9 ቢሊየን ብር እንደሚደርስ በተደረገ ጥናት ተረጋገጠ።

ከዚህ በቢሊዮን ከሚቆጠር ገንዘብ ውስጥ በአብዛኛው በዱቤ ሽያጭ የሚከናወን መሆኑም ተገልጿል። በዚህም ምክንያት ለመንግሥት የገንዘብ ፍሰት ላይ እጥረት መፍጠሩ እየተነገረ ነው፡፡

በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይህንን 9 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ በዛም አስቸጋሪ  እንደሆነ የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሀይለማርያም አስረድተዋል።
 አሰራሩ በመንግሥት ላይም ተጽእኖ መፍጠሩን ተከትሎ
ለነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ዱቤ ያለመስጠት አሠራር እንዲተገበር ተደርጓል።

LEAVE A REPLY