ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከ1996/97 ጀምሮ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር ተያይዞ 53 ቢሊዮን ብር የት እንደገባ ለማወቅ አለመቻሉ ተነገረ።
ለአራት ወራት በተካሄደ ጥናት የት እንደገባ በኦዲት ሊገኝ ያልቻለው ገንዘብን ጨምሮ የተለያዮ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቆመዋል በተባለው መሬት ላይ ሊገኙ አለመቻላቸው ተደርሶበታል።
“ባካሄድነው ጥናት እንዳረጋገጥነው ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ወጪ ተደርጓል የተባለ 53 ቢሊዮን ብር ለምን ወጪ እንደተደረገ የሚያሳይ ሰነድ ለም። የፌደራል ኦዲተሮችም ሰነድ አጥተው ኦዲት ሊደረግ አይችለም ብለው ትተውታል። ታስቦበት ማረጋገጫ እንዲጠፋ ተደርጓል” ሲሉ የጥናት ቡድኑ መሪ ዶክተር ቱሉ ገልጸዋል።
እያንዳንዳቸው እስከ 30 ቤቶችን ሊይዙ የሚችሉ 28 ሕንጻዎች (ብሎኮች) ሳይገነቡ ቀርተዋል ያለው የጥናት ቡድኑ፤ “እነዚህ ያልተገነቡ ሕንጻዎች ለመገንባት ከተቋራጮች ጋር ስምምነት ተደርሶ ነበር። እነዚህ ቤቶች ለምን ሳይገነቡ እንደቀሩ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ወይም የኮርፖሬሽኑ ቦርድ የያዘው ቃለ ጉባኤ የለም። ክፍያ መፈጸሙን ወይም አለመፈጸሙን የሚያሳይ ሰነድ ጠፍቷል። ይህ የሚያመላክተው ክፍያ ሳይፈጸም እንደማይቀር ነው” ሲልም ዝርፊያውን ጠቁሟል።