ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ደብረ ታቦር ከተማ ያላትን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ለመጠቀምና የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየተሠራ ነው ተባለ።
ከሆቴልና ቱሪዝም ጋር በተያያዘም ባለሀብቱ በዘርፉ እንዲሰማራ የቦታ አቅርቦት ተግባራትን እየተከናወነ ነው ያለው የደብረ ታቦር ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ፤ 60 የሚጠጉ ፕሮጀክቶች ወደ ተለያዩ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ለማስገባት እንቅስቃሴ መጀመሩንም ይፋ አድርጓል።
የከተማዋ ተወላጅ ባለሀብቶች ከተማዋን ይበልጥ ለማሳደግ በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየሰራ መሆኑን ያስታወቀው የከተማ አስተዳደሩ ከሆቴልና ቱሪዝም ጋር በተያያዘም ባለሀብቱ በዘርፉ ላይ እንዲሰማራ የቦታ አቅርቦት ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡