ኦፌኮ መንግሥት በእነ ጃዋር መሐመድ ጉዳይ ታሪካዊ ስህተት እየሠራ ነው አለ

ኦፌኮ መንግሥት በእነ ጃዋር መሐመድ ጉዳይ ታሪካዊ ስህተት እየሠራ ነው አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ለአስራ አምስት ቀን የረሀብ አድማ ላይ የሚገኙት እነ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ አሐምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ የጤና ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) መግለጫ አወጣ።

የእሰረኞቹ ሁኔታ በእጅጉ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለው ኦፌኮ፤ ለሚጠፋው የዜጎቻችንና አባሎቻችን ሕይወት መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል ሲልም አስጠንቅቋል።
“የፖለቲካ እሰረኞቹ ታመዋል፣ ከዚያም በላይ ሰው መለየት አይችሉም። መቆም አይችሉም። ሕይወታቸው አስጊ ደረጃ ነው” ያሉት የኦፌኮ ጽ/ቤት ኃላፊ፤ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ፊርማ በማሰባሰብ፣ አቤቱታ በማሰማት፣ ሰልፍ በማድረግ ወይም መንግሥታቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድር በማድረግ የእስረኞቹን ሕይወት ያድንልን ሲሉ ተማጽነዋል።
እስረኞቹ ምንም ቃል ማውጣት አይችሉም። የሕክምና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ያሉት የኦፌኮ አመራር፤ “ሰኞ እለት አይቻቸዋለሁ፤ ቃል ማውጣት አይችሉም፤ መቆም አይችሉም። ጀዋር መሐመድን እናቱ ሊጠይቁት ሄደው ሊለያቸው አልቻለም። ጀዋር መሬት ይዞ እየዳኸ ነው ወደ እስር ክፍሉ የሄደው። አልቅሼ ነው የተለየሁት” ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ገዢው ፓርቲ እየፈጸመ ያለው በኢትዮጵያ ታሪክም ጥቁር ነጥብ መሆኑን ተገንዝቦ፤ ለመንግሥት አስፈላጊውን ማስጠንቀቂያ እና ምክር እንሰጣለን ብሏል ኦፌኮ በመግለጫው።

LEAVE A REPLY