ሐሰተኛ የብር ኖት ሠርተው ወደ ገበያ እንዲገባ ያደረጉ ሁለት ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ሥር...

ሐሰተኛ የብር ኖት ሠርተው ወደ ገበያ እንዲገባ ያደረጉ ሁለት ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሐሰተኛ የብር  ኖት በመሥራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ ከነበሩ 3 ኢትዮጵያዊያን ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ።

ዮሴፍ ተከስተ ብርሃን እና ተክለ ብርሃን ገ/መስቀል የሚባሉ ት ሁለት ግለሰቦች ከሌላ አንድ ባልደረባቸው ጋር በመተባበር ሐሰተኛ ብሩን ሲያትሙ፣ ሲያሰራጩ እንደነበር ጉዳዮን የያዘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ጥብቅ ክትትል እና ድንገተኛ ፍተሻ 40 ሺሕ ሐሰተኛ ባለ 100 ብር የገንዘብ ኖቶች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY