ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአውሮፓ የኢኮኖሚ አቅሟን እያፈረጠመች በመጣችው በቱርክ አንካራ የተገነባው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛሬው እለት መመረቁ ተሰማ።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቩሉት ካቩሶግሉ መገኘታቸው ተነግሯል።
ኤምባሲው በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ መሰረተ ድንጋዩ ተቀምጦ ባለፉት አራት ዓመታት በግምባታ ላይ መቆየቱ አይዘነጋም።