ምርጫ ቦርድ የኦብነግ አመራሮች ውዝግብን በተመለከተ ውሳኔ አሳለፈ

ምርጫ ቦርድ የኦብነግ አመራሮች ውዝግብን በተመለከተ ውሳኔ አሳለፈ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ውዝግብ ውስጥ የከረሙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) አመራሮችን አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ አሳለፈ።

በእነ አቶ ራያል ሃሙድ በኩል ከጥር 12-15 ቀን 2013 ዓ.ም. ተካሂዷል የተባለው አስቸኳይ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ስለመጠራቱ የሚያሳይ ሰነድ ያልቀረበ መሆኑን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አረጋግጧል።
ተደረገ በተባለው አስቸኳይ ስብሰባው ላይ ተገኙ ከተባሉት 47 ሰዎች መሃል 10 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ብቻ በመሆናቸው በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀፅ 11.2 እና በአንቀፅ 13.1 መሠረት ምልአተ ጉባኤ ሳይሟላ የተካሄደ ስብሰባ መሆኑንም የቦርዱ መርማሪ ኮሚቴ ገልጿል።
በእለቱ የተካሄደውን ስብሰባ የመሩትና የፓርቲው “ምክትል ሊቀመንበር” እንደሆኑ የተገለፁት አቶ ራያል ሃሙድ በቦርዱ ጽሕፈት ቤት በሚገኘው የፓርቲው ሰነድ ላይ የሚታወቁት በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንደሆነና፤ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ አህመድ ያሲን ሼክ ኢብራሂም መሆናቸውን ምርጫ ቦርድ በውሳኔው ላይ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY