ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣው አዋጅ ተፈጻሚ መሆን እንዳልጀመረ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየካቲት 2012 ዓ.ም የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቢያፀድቅም፤ አዋጁ እስካሁን ተፈጻሚ ሲሆን ካለመታየቱ ባሻገር፤ በአዋጁ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን የሚጥሱ ድርጊቶች እየተፈጸሙ እርምጃ እየተወሰደ አለመሆኑ ጉዳዮን አስመልክቶ በተደረገው ውይይት ላይ ተነስቷል።
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ በላይሁን ይርጋ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣው አዋጅ እስካሁን ተፈጻሚ ያልሆነው በቅድሚያ ስለ አዋጁ ግንዛቤ መፍጠር በማስፈለጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአዋጁ ዙሪያ የግንዛቤና የስርዓት ሥራ ሊጀመር በታሰበበት ጊዜ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከሰቱ ግንዘቤ የመፍጠር ሥራው ሊሳካ አልቻለም ተብሏል።