ኢትዮጵያ ነገ ዜና || እሁድ ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ በጥይት ተመትተው የተገደሉት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አባል ላይ ቀደም ሲል ዛቻና ማስፈራሪያ ተፈጽሞባቸው እንደነበር የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ገለጹ።
የኢዜማ የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ግርማ ሞገስ እሁድ ዕለት መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ በጥይት ከመገደላቸው ቀደም ብሎ ማስፈራራሪያ ይደርሳቸው ነበር ያሉት የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው፤ አቶ ግርማ ቀደም ሲል በአካባቢው ከሚያደርጉት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስባቸው እንደ ነበር አስረድተዋል።
የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ፤ ከዚህ በፊት ከመምህር ግርማ ጋር ግጭት የነበራቸው ግለሰቦች ያስፈራሯቸው እና ይዝቱባቸው እንደነበር የሚያሳይ መረጃ መገኘቱን ተከትሎ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ያደርሱ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደ ነው ብሏል።