ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በረራ ማቋረጡን ተከትሎ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ 147 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማጣቱን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤርፖርች ድርጅት በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በነበረው የህግ ማስከበር እርምጃ ጋር ተያይዞ ዘጠኝ በሚሆኑ የበረራ ማዕከሎቹ በረራ በማቆሙ ምክንያት ከፍተኛ ጥቅሙ እንደተጓደለበት ጠቁሟል።
ተቋሙ ማግኘት የሚገባውን አንድ መቶ አርባ ሰባት ሚሊየን ስደሰት መቶ አርባ ሺሕ ሁለት መቶ ሃያ ሶስት ብር ማጣቱ የተረጃገጠው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባደረገው ምርመራ ግኝት እንደሆነም ተገልጿል።
ከጥቅምት 24 ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ኤርፖርት ድርጅት ወደ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ላሊበላ፣ ሰመራ፣ ሽረ፣ መቀለ እና አክሱም ከተሞች የሚያደርገው በረራ መቋረጡ ይታወሳል።