ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአስከፊው የሳዑዲ እስር ቤቶች ለረዥም ጊዜ የቆዮ 336 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መግባታቸው ታወቀ።
ወደ ሳዑዲአረቢያ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ተይዘው በሳዑዲ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የስደተኞች ማቆያ ጣብያ ውስጥ እና እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ስደተኞችን ወደ አገር መመለስ የተጀመረው ከወራት በፊት መሆኑ አይዘነጋም።
ዜጎችን በስፋት ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጠቆመው በሪያድ – ሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ በቀጣዮቹ አራት ሳምንታት ውስጥም ከሠባት መቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ቤት ለማምጣት ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል።