በኢትዮጵያ ነዳጅ የማደል ሥራ አትራፊ አይደለም ተባለ

በኢትዮጵያ ነዳጅ የማደል ሥራ አትራፊ አይደለም ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ ነዳጅ የማደል ሥራ አትራፊ እንዳልሆነ እና በመስኩ የተሠማሩ ድርጅቶችም ደስተኛ አለመሆናቸውን የኢትዮጵያ የነዳጅ አዳዮች ማህበር ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ላይ ይፋ አድርጓል።

ለነዳጅ ኩባንያዎች ይቋረጣል የተባለው የዱቤ ሽያጭ በካሽ መሆኑ ልንሰራው አንችልም ያለው ማኅበሩ፤ ቶታል ኢትዮጵያ በሚያከራየው ማደያ 70 በመቶ የቤት ክራይ  መጨመሩንም ገልጿል።
አንዳንድ የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች ያከራዩትን ማደያ ካፌውን ላቢያጆ  እና ሌሎች አገልግሎት መስጫ  ለማከራየት  መታሰቡን  የጠቆመው ማኅበሩ፤ የአዳይ እና የኩባንያው  ስምምነት የመንደር ውል መሆኑንም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ከዘይቱ ትርፍ ባገኝበትም በተለያዩ ቦታዎች ከማደያ ውጭ የሚስተዋለው የመሸጫ ዋጋው የማይገባ እንዲሆን አድርጎታል ሲልም ተሰምቷል።
በነዳጅ ጉዳይ ላይ የሚመለከተውም ሆነ መንግሥት ማህበሩን ለማነጋገር አልቻለም ተብሏል። ማህበሩ የነዳጅ ዱቤ ቀርቶ 16 በመቶ ከባንክ ተበድሮ ሥራውን መሥራት አስቸጋሪ እንደሆነም አስረድቷል።
የነዳጅ ጉዳይ ላይ የባሰ ቀውስ እንዳይፈጠር መንግሥት በብርቱ ማጤን አለበት፣ መንግስት መልስ የማይሰጥ ከሆነ ከሚመለከታቸው ጋር እመክራለሁ ሲልም ማኅበሩ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

LEAVE A REPLY