ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የቀድሞው የአረና ፓርቲ አባል እና ከአንድ አመት በፊት አዲስ አደረጃጀት ሆኖ ብቅ ያለው የፈንቅል አመራር የነበረው የማነ ንጉሥ ትግራይ ውስጥ ተገደለ።
ትናንት ከቀኑ 10 ሰዐት ገደማ የማነ ንጉሥ በአፈቃሪ ሕወሀት ተጠቂዎች መገደሉን ከመቀሌ ጊዜያዊ አስተዳደር ምንጮች ገልፀዋል።
ወደ መቀሌ በሚወስደው እና አላጄን አለፍ ብሎ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ባላት “ሂዋነ” በተባለች ከተማ የተገደለው የማነ በስፍራው ተገኝቶ መጋዘን ውስጥ የነበረ እህል በማከፋፈል ሥራ ላይ እንደነበረ ምንጮቹ አረጋግጠዋል።
ከየማነ ጋር የነበሩ ሁለት የመከላከያ አባላት ላይ ተመሳሳይ ግድያ እንደተፈፀመባቸው የጠቆሙት ምንጮች ቦታው የየማነ የትውልድ መንደር እንደሆነም ገልጸዋል።
ዛሬ ኢቲቪን ጨመሮ የተለያዩ የመንግሥት የመገናኛ ብዙሀን የየማነን መገደል በይፋ ዘግበዋል።