ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በእምነታቸው እንዲተጉ ከማንቃት ባሻገር በተለያዮ የሀገሪቱ ክልሎች በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተፈጸሙትን ጥቃቶች በማውገዝ የሚታወቀው መምህር ምህረት አብ አሰፋ ትልቁን የስብከት መርሀ ግብር ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ።
የሃይማኖት መምህሩ የማንቂያው ደወል በጃንሜዳ ከአዲስ አበባ ጎልማሶችና ማኀበራት ሕብረት ጋር በመተባበር የካቲት 21/2013 ከቀኑ 6 ሰዐት ጀምሮ “ለመደወል” አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቋል ነው የተባለው።
ብዙ ሺሕ ምዕመናን ይገኝበታል ተብሎ በሚጠበቀው ታላቁ የስብከት ፕሮግራ ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ይሰበካል፣ ያሉት የፕሮግራሙ አዘጋጆች ታዋቂ ዘማሪያን እና የሰንበት ት/ቤት አባላትም እንደሚሳፉ ገልጸዋል።