ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለጹ።
“በየስድስት ወሩ የምናካሂደውን እያንዳንዱን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የሥራ ክንውን ግምገማ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ጋር በመሆን ጀምረናል” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስነብበዋል።
በጸደቀው ዓመታዊ ዕቅድ መሠረት ቀጣይነት ያለውን ምዘና መከወናችን፣ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በመሙላት እና አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ለዜጎች ተገቢው አገልግሎት መቅረቡን ለማረጋገጥ ያስችላል ያሉት የብልጽግና መሪ መንግሥታቸው የዜጎችን መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላት በእጅጉ እየጣረ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።