ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን የኦሮሚያ ልዩ ኀይል የአካባቢውን ማኅበረሰብ እና አርሶ አደሮችን ትጥቅ እያስፈታ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ አዲስ ማለዳ ዘግቧል።
በአካባቢው በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚሰነዝረው የኦነግ ሸኔ ጦር በስፋት የሚንቀሳቀስ ቢሆንም ነዋሪው በግድ ትጥቁን እንዲፈታ እየተደረገ ነው።
የክልሉ ልዩ ኀይል ማኅበረሰቡን ትጥቅ ማስፈታት የጀመረው ካለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ልዩ ኃይሉ ማኅበረሰቡ እራሱን ከኦነግ ሸኔ ጥቃት የሚጠብቅበትን መሳሪያ በግድ እያስፈታ ነው በማለት ቅሬታቸውን የጠቆሙት እነዚህ ነዋሪዎች፤ ከወዲሁ ስጋት ላይ መውደቃቸውን እና ለሚደርስባቸው ጉዳት የክልሉ መንግሥት ሓላፊነቱን እንደሚወስድ ገልጸዋል።