ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከቅርብ ቀናት ወዲህ በአዲስ አበባ የተከሰተውን የነዳጅ እጥረት ተከትሎ በክልሎች ከተሞች ነዳጅ በጥቁር ገበያ እስከ 70 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑ ተነገረ።
በአገራችን የተለያዩ የክልል ከተሞች አንድ ሊትር ነዳጅ በጥቁር ገበያ ከ50 ብር እስከ 70 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን አሽከርካሪዎች እየገለጹ ናቸው።
በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ በአገር ዐቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን ተከትሎ ነዳጅ በጥቁር ገበያ በውድ ዋጋ እየተሸጠ ነው ያሉ አሽከርካሪዎቹ ይህንንም ለማግኘት ከፍተኛ የሆነ ሰልፍ መጠበቅ ግድ እንደሆነ አስረድተዋል።