ወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ እስር ላይ ስሚገኙ የኦነግ አመራሮችን ከፍ/ቤት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን...

ወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ እስር ላይ ስሚገኙ የኦነግ አመራሮችን ከፍ/ቤት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በእስር ላይ የሚገኙ የኦነግ አመራሮችን እስር በተመለከተ ‘ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ ገለጹ።

ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያሉ እስረኞች በመጪው ምርጫ ለመወዳደር በእጩነት መመዝገብ አይችሉም ያሉት ብርቱኳን፤ በዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ፤ በፍርድ ቤት ጉዳያቸው የተዘጋ ፣ እንዲሁም ዐቃቤ ሕግ የማቀርበው ክስ የለም ያላቸው ነገር ግን በእስር ላይ የሚገኙ የኦነግ አባላት መኖራቸውንም አስታውሰዋል።
በሕግ መብታቸው ያልተገፈፈ፣ ግን በእስር ላይ የሚገኙ አባላትን በዕጩነት ማቅረብ ይቻላል ወይ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ፤ “በፍርድ ቤት ጉዳይ የሌላቸው፤ ነገር ግን በእስር ላይ የሚገኙ፣ በተለይም የኦነግ አመራሮችን በተመለከተ ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገርን ነው” ብለዋል።

LEAVE A REPLY