ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአውሮፓ ኅብረትና የጀርመን መንግሥት በጋራ ያበረከቱለትን 22 መኪኖች መረከቡ ተሰማ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በትላንትናው ዕለት ከአውሮፓ ሕብረትና ከጀርመን መንግሥት በጋራ ለቦርዱ የተበረከቱትን 22 መኪኖች ተረክበዋል።
የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በተገኙበት የተፈጸመው ርክክብ 12 ሃርድ ቶፕ እና 10 ፒክ አፕ መኪኖችን ያካተተ ሲሆን፤ ዋና ሰብሳቢዋ ቦርዱ የሎጀስቲክ እንቅስቃሴ ላይ ያለበትን ውስንነት ጠቅሰው፣ ለተደረገው ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል።