ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ሱዳን ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በራሳችን ገንዘብ ነዳጅ እና ዳቦ እንኳ ለመግዛት ተከልክለናል አሉ።
በካርቱም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በዓለም ዐቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት የስደተኛ እውቅና አግኝተው ለረዥም ዓመታት በከተማው የኖሩ ቢሆኑም የአገሪቱ ፖሊስ እንግልት እያደረሰባቸው መሆኑን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
በተለይም ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር ይገባኛል የተነሳ ውዝግብ ውስጥ ከገቡ በኋላ ደግሞ በብዙ ፍራቻና ስጋት ውስጥ እየኖርን ነው የሚሉት ስደተኞች ከኢትዮጵያ በተለያየ ምክንያት የወጡና ለአመታት የኖሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።