ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባን ወደ መጋቢት 16 መቀየሩን ገለጸ

ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባን ወደ መጋቢት 16 መቀየሩን ገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ የሚመራው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ቀደም ሲል ከተያዘለት የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም መቀየሩን አስታወቀ።

ቦርዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የቻለው ከሀገራዊ ምርጫው ጋር ተያይዞ የተለያዮ ችግሮች በአፈጻጸም ደረጃ መከሰታቸውን ተከትሎ ነው።
 የምርጫ ክልል ቢሮዎች ዝግጅት መዘግየት እና አስፈጻሚዎች ሰልጥነው ከተሰማሩም በኃላ ቢሆን ቢሮዎች ዝግጁ ሆነው ባለመገኘታቸው የቢሮ መከፈት መዘግየቱ፣ ዋነኛ እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል ተቋሙ አስታውቋል።
 የእጩዎች ምዝገባ በጊዜ ሰሌዳው መሰረት መጀመር አለመቻሉ እና ለሁለት ዙር መከፈሉ፣ የፕሮግራም ለውጥ ለማድረግ አስገድዶኛል ያለው ምርጫ ቦርድ፤ በተመሳሳይ
 የእጩዎች ምዝገባ ሂደትን በመገምገም፣ ተጨማሪ ቀናት እንደሚያስፈልገው በመረዳት በመጀመሪያ ዙር የእጩዎች ምዝገባ በተጀመረባቸው ክልሎች ለ4 ቀናት ያራዘመ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY