የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት የፊታችን እሁድ ኢትዮጵያ ይገባል ተባለ

የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት የፊታችን እሁድ ኢትዮጵያ ይገባል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ዓለምን ክፉኛ እያስጨነቀ የሚገኘው የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት የፊታችን እሁድ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ ተነገረ።

የመጀመሪያው ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት በመጪው እሁድ ወደ ሀገር ቤት ይገባል ያለው የጤና ሚኒስቴር፤ በቀጣይ ወራቶችም ተጨማሪ የቫይረሱ መከላከያ ክትባቶች ይገባሉ ሲል ገልጿል።
በዓለም የጤና ድርጅት እና የተለያዩ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ጥምረት የተመሰረተው  ኮቫክስ በኩል ክትባቱ መገኘቱን ጤና ሚኒስቴር አረጋግጧል።
የጤና ሚኒስቴር በ2 ወራት ጊዜ ውስጥ 9 ሚሊየን ዜጎችን ለመከተብ የሚያስችል ክትባት እንደሚረከብም እወቁልኝ ብሏል።

LEAVE A REPLY