ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኢትዮጵያ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ አሜሪካ በሉዓላዊ አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ጠይቋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት ማሪያ ዛካሮቫ አሜሪካ በአገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የምታደርገውን ጥረት መቃወማቸውን ይፋ አድርገዋል።
በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት አባል አገራት ከሆኑት መካከል ሦስት የአፍሪካ አገራት ረቂቅ መግለጫውን መደገፋቸውን ያጋለጠው አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ፤ ሀገራቱ ኬንያ፣ ቱኒዚያ ኒጀር መሆናቸውንም ጠቁሟል።