ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ወልቃይትና የራያ አካባቢዎችን በተመለከተ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያቀርበው ጥያቄ ካለ፤ በሕጋዊ መንገድ ማቅረብ ይቻላል ሲል የአማራ ክልል ገለጸ።
“የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያነሳው ጥያቄ ተገቢነት የሌለው ክስ እና ውሃ የማይቋጥር ነው” ያሉት የአማራ ክልል የመንግሥት ጉዳዮች ኮሚዮኒኬሽን ሓላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ፤ ጥያቄውን አስተዳደሩ በሕግ አግባብ ለፌደራል መንግሥቱ ማቅረብ ይችላል ብሏል።
የአማራ ክልል ይህን ይበል እንጂ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ሓላፊ አቶ ገብረ መስቀል ካሳ በአማራ ክልል ኃይሎች የክልሉ ግዛቶች የተያዙ በመሆኑ፤ አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ይናገራሉ።