ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን በተመለከተ ያደረገው ውይይት ከስምምነት ላይ ሳይደርስ መቋረጡ ተሰማ።
የጸጥታው ምክር ቤት ያካሄደውን ውይይት ተከትሎ ከስምምነት ቢደርስ ኖሮ ኢትዮጵያ በተመለከተ የቀረበው ረቂቅ መግለጫን ይፀድቅ ነበር እንደ ነበር ዓለም ዐቀፉ የዜና ተቋሙ ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።
የመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ መልኩ በትግራይ አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ እና ግጭት እንዲቆም የሚጠይቅ ነበር የሚለው የዜና ተቋሙ፤ ይሁን እንጂ ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣን ካላቸው አምስት ቋሚ የምክር ቤቱ አባላት መካከል የሚገኙት ሩሲያ እና ቻይና መግለጫው በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው ሲሉ ተቃውመዋል ብሏል።