ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት አቶ መስጠፌ ሙሀመድ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው መገለጫ ሰጡ።
በሰጡት መግለጫ “የሶማሌ ክልል ህዝብ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከመንፈቅ ከነበረው ጭቆና ተላቆ የነጻነት አየር እየተነፈሰ ነው። የራሱን የፖለቲካ ፍላጎት በግልጽና በነጻነት መናገር የቻለበት ሁኔታ ተፈጥሯል፣ በሱማሌ ክልል የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፊ ነው፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፤ በክልሉ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩል የሚያሳትፍ ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር ነው ያለው፣ በፖለቲካ መፎካከር እንደተጠበቀ ሆኖ ፉክክሩ ግን ሀገርን ወደ ማፍረስ ህዝብን ወደ ማጋጨት መሄድ የለበትም ብለዋል።
ቀደም ሲል የኮንትሮባንዲስቶች ኔት ወርክ የፖለቲካና የጸጥታ ክፍሎችን ሁሉ ያካተተ ስለነበር በክልሉ ሰላምና ጸጥታ ላይ ስጋት ፈጥሮ ነበር። ያሉት ፕሬዚደንት ሙስጠፌ የእብሪት፣ የስግብግብነትና የዘረኝነት አካሄድ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ይሳካ እንደሆነ እንጂ ዞሮ ዞሮ መጥፊያ እንደሚሆን በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ከህወሓት በላይ ምሳሌ የሚሆን የለም።… ዓድዋ ድል ሲመዘገብ እንደነበረው አገራዊ አንድነት አሁንም የአገራችን ህዝቦች በአንድነትና በትብብር መንፈስ ከሰሩ፤ ልዩነቶችን አጥብበው መግባባት ከቻሉ፤ እጅ ለእጅ ከተያያዙ፤ ከጽንፈኝነት ነጻ የሆነ የፖለቲካ አስተሳሰብ ከሰፈነ ከዓድዋ በላይ ሌሎች ድሎች ማስመዝገብ እንችላለን” ሲሉ ተናግረዋል።