ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና በበሽታው ተጠቅተው ህይወታቸው የሚያልፍ ዜጎች ቁጥር ከእለት እለት እየጨመረ መምጣቱን የተናገረው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነው፡፡
በአሁን ሰዓት በአገራችን በቀን ከሚመረመሩ 100 ግለሰቦች 20 ያህሉ ወይም 20% የኮቪድ-19 ቫይረስ እንዳለባቸው የሚያሳይ ውጤት እየተመዘገበ ነውም ተብሏል፡፡
በዚህም በሀገራችን ያለው የኮሮና ቫረስ ስርጭት መጠን በ12 ነጥብ 8 በመቶ የጨመረ ሲሆን፣ በአፍሪካ ደረጃ ደግሞ በ10 በመቶ መጨመሩን እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ በ2 በመቶ መጨመሩን ኢንስትቲዩቱ አስታውቋል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህን በከፍተኛ ሁኔታ ስርጭቱን እየጨመረ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚረዱ ጥንቃቄዎችን በማድረግ ራሱንና ወገኑን እንዲጠብቅ ኢንስትቲዩቱ በማህበራዊ የትስስር ገጹ አሳስቧል፡፡