ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ቃለ አቀባይ የሆኑት ጄን ሳኪ ለጋዜጠኞች በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ ነው ይሀንን የተናገሩት።
ከትግራይ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አሜሪካ ልትወስድ ስለምትችለው ተጨማሪ እርምጃ ከጋዜጠኛ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ አሜሪካ በዲፕሎማቶቿ አማካኝነት እስካሁን የሔደችውን ርቀት አንስተዋል።
በትግራይ ያለው ሁኔታ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ‘’እጅግ ያሳስባቸዋል፤ በቅርበትም እየተከታተሉት ነው” ብለዋል።
“የባይደን አስተዳደር በክልሉ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ እንዲሻሻል የእርዳታ ሰራተኞችን ወደ ክልሉ እንዲገቡ ከማድረግ በተጨማሪ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ ነው” ሲሉም ገልፀዋል፡፡