ኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋር ሀገር መሆኗን የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋር ሀገር መሆኗን የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እንደሚያሳስበው የገለጸው የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋር አገር መሆኗን ገለጸ።

ምክር ቤቱ፣ መንግስት ከአፍሪካ ህብረት ጋር ለመተባበር ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚያበረታታ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ማሻሻያ ማድረጓን የጠቀሰው የህብረቱ መግለጫ፣ በቀጣይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ገንቢ ውይይት ማድረግ እንደሚፈልግ አስታውቋል። በተጨማሪም፣ ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫን ግልጽ እና ተዓማኒ በሆነ መልኩ ለማካሄድ መንግስት የያዘውን አቋም ምክር ቤቱ በመግለጫው አድንቋል፡፡

LEAVE A REPLY