ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በዘንድሮው ምርጫ ለመሳተፍ 8209 የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች እንደተመዘገቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ለምርጫው ከተመዘገቡ 49 ፓርቲዎች 47ቱ ዕጩዎቻቸውን መቅረባቸውን የገለፀው ቦርዱ 125 የግል ዕጩዎች መመዝገባቸውንም ተናግሯል።
እስካሁን 8209 እጩዎችን ለክልል እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመዝገቡን ይፋ ያደረጉት የቦርዱ ሠብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ እጩዎች በማስመዝገቡ ሒደት የአስፈጻሚዎች በምርጫ ጣቢያዎች አለመኖር፣ የምርጫ ጣቢያዎች ሳይከፈቱ መዘግየት፣ የፀጥታ ችግሮች፣ የእጩዎች መታሰር ከአጋጠሙ ችግሮች መካከል እንደሚገኙበት አመልክተው፣ የእጩ ምዝገባው በሁለት ዙር መካሄዱንም ገልፀዋል።