ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአማራ ክልል ከ30 ዓመት በላይ ሲጠቀምበት የነበረው ሰንደቅ ዓላማ እንዲቀየር የክልሉ ምክር ቤት ወሰነ።
ምክር ቤቱ “ሰንደቅ ዓላማው አንድን ፓርቲ እንጂ የክልሉን ባህል፣ ልምድ፣ ጀግንነት እና እሴት አይወክልም” በሚል ነው እየተካሄደ ባለው 17ኛ መደበኛ ጉባዔ ሰንደቅ ዓላማው እንዲቀየር የቀረበውን አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ያፀደቀው።
ሰንደቅ ዓላማው የቅሬታ ምንጭ ሆኖ መቆየቱንም የምክር ቤት አባላት አመልክተዋል። ከ6 ወራት በኋላ የአማራ ክልል የህዝቡን ስነልቦና ያገናዘበ፣ የክልሉን ህዝብ እሴትና ማንነት ያቀፈና በአብዛኛው የክልሉ ህዝብ ተቀባይ የሆነ ሰንደቅ ዓላማ እንደሚኖረውም በምክር ቤቱ መግለጫ ተመልክቷል።