በአሜሪካ የቀረበው ክስ “የሀሰት ውንጀላ” መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ!

በአሜሪካ የቀረበው ክስ “የሀሰት ውንጀላ” መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መጋቢት 01/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ለኮንግረሱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሰጡት መግለጫ በትግራይ ላይ የዘር ማጽዳት ድርጊት ተፈጽሟል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

በትግራይ ክልል ከሕግ ማስከበር ዘመቻው በፊትም ሆነ በኋላ አንድ አካል ላይ ትኩረት ተደርጎ ምንም ዓይነት የዘር ማጽዳት ድርጊት እንዳልተፈጸመ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አትቷል። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ሙሉ ለሙሉ ክሱን አይቀበለውም ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን ፖለቲካዊ ከሚያደርጉ አካላት ውጪ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ አጋሮች ጋር ፍትሕ እንዲሰፍን እና የማጣራት ሂደቱ በፍጥነት እንዲከወን ግልጽ አቋሙን ይፋ ማድረጉንም አስታውሷል መግለጫው።

ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመታት አሁን ካለው የአሜሪካ መንግሥት አስተዳደር ጋር ስትራቴጂክ የሆነ የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክራ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግላጫ አመላክቷል። ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው ለውጥ አሜሪካ ስለምታደርገው ድጋፍም አመስግኗል።

LEAVE A REPLY