በባንኮች ጭምር የሚታገዝ “የአገሪቱን ኢኮኖሚ የመረበሽ ህገወጥ ዘመቻ” መጀመሩ ተገለጸ!

በባንኮች ጭምር የሚታገዝ “የአገሪቱን ኢኮኖሚ የመረበሽ ህገወጥ ዘመቻ” መጀመሩ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በመቀሌ ከተማ ህገ-ወጥ ገንዘብ ሲያትሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

በህግ ማስከበር ስራ ላይ የተሰማራው የመከላከያና ፌደራል ፖሊስ ኃይል ባደረጉት ክትትል ሕገ-ወጦቹ ከ570 ሺህ ብር በላይ ተመሳስሎ የተሰራ ብር በማተም ወደ ህብረተሰቡ ለማሰራጨት ሲያዘጋጁ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ህገወጥ አታሚዎቹ በርካታ ገንዘብ ወደ ሁመራ፣ የድንበር አካባቢና ሌሎች ቦታዎች ያሰራጩ በመሆኑም ተረጋግጧል።

ግለሰቦቹ ህጋዊ ንግድ ፈቃድን ከላላ በማድረግ ሕገ-ወጥ ተመሳስሎ የተሰራ የኢትዮጵያ ብር፣ የኤርትራ ናቅፋ እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦችን በማተም ህብረተሰቡን የማሳሳትና የአገሪቱን ኢኮኖሚ የማናጋት ስራ ሲሰሩ እንደነበርና በአሁኑ ወቅትም የሕወሓት ቡድንና ተላላኪዎቹ በተመሳሳይ ሕገ-ወጥ ተግባር ላይ በስፋት መሰማራታቸው መረጋገጡም ተመልክቷል።

የህግ ማስከበር ዘመቻው መሪ ኮለኔል ካሳ መላኩ በሰጡት መግለጫ “በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ህገ-ወጥ ገንዘቦቹን በአማራና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎችና በሱዳንና ኤርትራ ድንበር አካባቢዎች ማሰራጨታቸውን ተናግረዋል።  ህገ-ወጥ ገንዘቦቹን ወደ ህብረተሰቡ ለማሰራጨት ትብብር የሚያደርጉ የተወሰኑ የግል ባንኮችም መኖራቸውን ጠቁመዋል።

LEAVE A REPLY