ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ዛሬ ባካሄደው ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤው አዲስ ሊቀመንበር እና የምክር ቤት አባላት መምረጡን አመልክቶ ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት በመጪው ምርጫ ለመወዳደር መዘጋጀቱን አስታውቋል።
ኦነግ ለሁለት ቀናት ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤው አቶ አራርሶ ቢቂላን የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን የገለፀ ሲሆን፣ ሕገ ደንቡን ማሻሻሉንና የስነ ስርዓት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታወቋል።