በሁለት የውጭ ዜጎች ተዘጋጅቶ በደብረጺዮን ስም ለአፍሪካ ህብረት ሊላክ የነበረ ደብዳቤ ተጋለጠ!

በሁለት የውጭ ዜጎች ተዘጋጅቶ በደብረጺዮን ስም ለአፍሪካ ህብረት ሊላክ የነበረ ደብዳቤ ተጋለጠ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በቀድሞ የትግራይ ልማት ማህበር ሰራተኛ በሆነችው ዶክተር ፊዮና ሜሃንና በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከ20 ዓመታት በላይ በሰራችው ጌል ጎርደን አማካኝነት ተዘጋጅቶ፣ በዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ስም ለአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ሊላክ የነበረ ደብዳቤ ምስጢር ተደረሰበት።

ኢትዮጵያ ዳይጀስት እንዳጋለጠው፣ እነዚህ ግለሰቦች እኤአ በማርች 12 /2021 ደብዳቤውን አርቅቀው ከጻፉ በኋላ ቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ለነበሩትና በአሁኑ ወቅት የጁንታውን ጉዳይ አሜሪካ ሆነው እየመሩ ላሉት ለአቶ ብርሀነ ገብረክርስቶስ መላካቸው ተረጋግጧል።

ሁለቱ ሴቶች እና ህወሓት ገና በትግል ላይ እያለ ጀምሮ ወዳጆች እንደነበሩ የገለጸው መረጃው፤  በዚህ ወዳጅነታቸውም የተነሳ እንግሊዛዊቷ ጌል ጎርደን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ተቀጥራ ለበርካታ አመታት አገልግላለች።

በተመሳሳይም ፊዮና የተባለችው የአየርላንድ ዜጋ ያላት ሴት ከህወሓት ጋር በረድኤት ድርጅት ስም በቀድሞ የትግራይ ልማት ማህበር ውስጥ አብራ ስትስራ የኖረች ናት ተብሏል። ይህ መረጃ እንደገለጸውም፣ እነዚህ ሁለት ሴቶች ለንደን እና ደብሊን ሆነው የጁንታውን የውጭውን ዓለም የውሸት መረጃ የሚያሰራጩና ዘመቻዎችን የሚያስተባብሩ መሆናቸው ተጋልጧል።

LEAVE A REPLY