ምርጫ ቦርድ አማራና ኦሮሚያን ጨምሮ ለአራት ክልሎች ማሳሰቢያ ሰጠ!

ምርጫ ቦርድ አማራና ኦሮሚያን ጨምሮ ለአራት ክልሎች ማሳሰቢያ ሰጠ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስድስተኛውን አገራዊ ምርጫን ደኅንነት ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ባደረጋቸው ውይይቶችና ንግግሮች መሠረት አብዛኛዎቹ የምርጫ ክልሎች ጥበቃ ሊሟላላቸው መቻሉን ጠቁሞ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሱማሌና በደቡብ ክልሎች 98 የምርጫ ክልሎች ጥበቃ ስላልተመደበላቸው በአስቸኳይ እንዲያሟሉላቸው አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያየ መልኩ እየተከሰቱ ያሉትን ተግዳሮቶች ለመቋቋም እየሰራ መሆኑን እየገለፀ ባለበት በአሁኑ ወቀት በደቡብ ክልል ታሥረው የነበሩ አቶ ሁሴን አባቴ እና አቶ አስቻለው ቡባ የተባሉ እጩ ተወዳደሪዎችን ለክልሉ በቀረበው ደብዳቤ መሰረት በትላንትናው እለት ከእስር መፈታታቸውን አስታወቋል፡፡

 

LEAVE A REPLY