የትህነግ ጦር አዛዦችና 110 ሚሊሻዎች ኮረም ላይ ተማረኩ፤ ተቆርጠው የቀሩት ውድመት አደረሱ!

የትህነግ ጦር አዛዦችና 110 ሚሊሻዎች ኮረም ላይ ተማረኩ፤ ተቆርጠው የቀሩት ውድመት አደረሱ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከመከላከያ ከድተው የከሀዲውን ሀይል ከተቀላቀሉና በአዋጊነት ሲሰሩ ከነበሩት መካከል ኮሎኔል ሀዲሽ ሁሉፍ፣  ሻለቃ ባሻ ጉኡሽና ሻምበል ጌታቸው ኮረም ላይ በተደረገ ከባድ ጦርነት ከ110 ሚሊሻዎች ጋር ተማርከዋል::

የቀድሞ የማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥና የጄኔራል አበባው ታደሰ ምክትል የነበረው ብርጋዴር ጀኔራል አብረሀ (ድንኩል) ደግሞ ከ8 ኮሎኔሎች ጋር መደምሰሱ ተረጋግጧል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ ቆርጠው የገቡ የትህነግ ተዋጊዎች ዋግ ላይ ጥቃት ማድረሳቸው የተሰማ ሲሆን፣ ቦራ ላይ በነበረው ጦርነት “የተወሰነው የተከዜን መስመር ተከትሎ ተቆርጦ ቀርቷል።

ይህ የህወሀት ሚሊሻ ትናንት ሌሊት ላይ በትንሽ ሚሊሻዎች የምትጠበቀዋን ጻታ የተባለች ትንሽ የወረዳ ከተማ በመውረር ክሊኒኮችን ሰብረው መድሃኒቶችንና የህክምና መሣሪያዎችን ዘርፈውና የእህል መጋዘኖችን ከዘረፉ በኋላ የተወሠኑትን አቃጥለዋል። የቴክኒክና ሙያ ቅርንጫፍ ተቋማትና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሰዋል” ሲል ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

“ይሁንና ዛሬ ምሳ ሰአት ላይ እነዚህ የትህነግ ትርፍራፊዎች በአማራ ልዩ ሃይል ድባቅ ተመተዋል” ያለው መረጃው፣ የአማራ ልዩ ሃይልን ተከትሎ የመከላከያ 21ኛ ክ/ጦር ወደ ከተማዋ ገብቶ የማረጋጋት ስራ መጀመሩንም አያይዞ ገልጿል።

LEAVE A REPLY