ለፖርቲዎች ምርጫ ቅስቀሳ የሚረዳ አዲስ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ!

ለፖርቲዎች ምርጫ ቅስቀሳ የሚረዳ አዲስ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ተሳታፊ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳቸውን ለማድረግ እንዲሁም ሀሳባቸውን ለህዝቡ እንዲሸጡ የሚያስችል “ምርጫዬ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያና ድረ ገጽ ማዘጋጀቱን እውነት ኮሙኒኬሽን ለኢትዮጵያ ነገ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት መራጮች ስለሚመርጡት ፓርቲ እና ስለተመራጩ ዕጩ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው ይህንን ፍላጎት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ መሸፈን ይቻል ዘንድ የሞባይል መተግበሪያና ድረ-ገጹ መዘጋጀቱን አመልክቷል።

“በተለይ የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ የምርጫ ቅስቀሳዎችን ለማድረግ ቴክኖሎጂውን እንደ ትልቅ አቅም መጠቀም ይገባል” ያለው ከአዘጋጆቹ የተላከልን መግለጫ፣ ሁሉንም ፓርቲ ያለምንም ክፍያ በእኩል ለማሳተፍ የሚያስችል መድረክ መመቻቸቱንም ጠቁሟል።

በምርጫ መተግበሪያው/ ድረ ገጹ ላይ የፓርቲዎች መግለጫ፣ የሲቪክ ማህበራት እና የመራጮች ምዝገባ፣ የእጩዎች መግለጫ፣ የምርጫ ቦርድ መረጃ፣ ለፓርቲዎች ድጋፍ የሚደረግበት የእርዳታ ወይም የልገሳ ፎርም፣ ሰነዶች እና ተቀሳቃሽ ምስሎች ማጋሪያ፣ ዜና፣ ወደ ማህበራዊ ገጽ ማጋሪያ እንዲሁም ኩነቶችን ማስተዋወቂያ ሊንኮች መካተታቸውንም ለመረዳት ተችሏል።

LEAVE A REPLY