ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት የ”ኦ” ደም አይነት እጥረት እንዳጋጠመው አስታውቋል።
ብሔራዊ ደም ባንክ ዛሬ እንደገለፀው፣ አሁን ላይ በክምችቱ የሚገኘው “ኦ” የደም አይነት ለሰባት ቀናት ብቻ የሚሆን ነው።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት “ኦ/O’ የደም አይነት ያላቸው ዜጎች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የደም ባንክ አገልግሎት ቅርንጫፍ በመሄድ ደም እንዲሰጡና ህይወት እንዲያድኑ” ሲልም ጥሪ ቀርቧል።