የሱማሌና አፋር ክልሎች አለመግባባት ወደአገራዊ ቀውስ እንዳይሻገር ተሰግቷል!

የሱማሌና አፋር ክልሎች አለመግባባት ወደአገራዊ ቀውስ እንዳይሻገር ተሰግቷል!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየሱማሌና አፋር ክልሎች ለአመታት ሲወዛገቡባቸውና ወደግጭት ሲያመሩባቸው በቆዩ 8 አዋሳኝ ቀበሌዎች ላይ ምርጫ እንዳይካሄድ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ መተላለፉ የሱማሌ ክልል አስተዳደርን አስከፍቷል።

የሱማሌ ክልል መንግስት “ውሳኔው ካልቸሻረ በምርጫው ለመሳተፍ እቸገራለሁ” የሚል መግለጫ እስከመስጠት ያደረሰው ሲሆን፣ ከውሳኔው ጋር ተያይዘው የታዩ ሁኔታዎችም ጉዳዩ ለሶማሌና አፋር ክልሎች አለመግባባት መንስኤ ከመሆን አልፎ ለአገራዊ ቀውስ ምክንያት እንዳይሆን ስጋት አሳድሯል።

“የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በማሊሌ እና በአፋር ከልል አዋሳኝ ቦታዎች የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችን ያወጣዉን መግለጫ አስመልክቶ ከሱማሌ ክልል የተሰጠው ውሳኔ” በሚል የሱማሌ ክልል ትናንት መጋቢት 16/2013 መግለጫ አውጥቷል።

“የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኣፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ8 የክልላችን ቀበሌዎች ላይ ያቀረበውን የይገባኛል አቤቱታ መነሻ አድርጎ በቀበሌዎቹ ሊከፈቱ የነበሩ 30 የምርጫ ጣቢያዎች በአካባቢው እንዳይቋቋሙ መወሰኑን ክልሉ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ ተመልከተናል።

ከአሁን በፊት የአፋር ከልላዊ መንግስት በክልላችን በሚገኙ ሶስት ከተሞች ወይም ቀበሌዎች ማለትም ገርባኢሲ (ገዳማይቱ) አዳይቱ እና ኡንዱፍን ላይ የይገባኛል ጥያቄ ያቀርብ የነበረ ሲሆን አሁን በተወሰነው ውሳኔ የተካተቱት ተጨማሪ አምስት ቀበሌዎች ቀርቶ ሶስቱ ቀበሌዎችም ክልሉ ከተመሰረተ ጀምሮ በሱማሌ ክልል ስር ሲተዳደሩ የቆዩ በመሆናቸው በቦርዱ የተወሰነው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም”ብሏል።

“የሱማሌ ከልላዊ መንግስት በቀን 12/06/2013 (TC MDDS/LU/68/917/2013.” ANCA . (114.0 ደብዳቤ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የይገባኛል ጥያቄ ያነሳባቸው 8 ቀበሌዎች ባለፉት 5 ብሔራዊ ምርጫዎች በሱማሌ ከልል ሥር ሆነው የፈደራል ምክር ቤት እና የከልል ምክር ቤት ተወካዮች ምርጫ የተካሄደባቸው መሆኑን በመጥቀስ 6ኛው ብሔራዊ ምርጫም ቀድሞ በነበረው መሠረት እንዲከናወን በአፅንኦት መጠየቁ ይታወሳል” በማለት አስታውሷል።

አያይዞ በመግለጫው ውሳኔው የክልሉን አስተዳደርና ህዝብ ማስከፋቱን ከዘረዘረ በኋላ፣ “…..ስለሆነም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተወሰነው ውሳኔ በሱማሌ ከልላዊ መንግስት በኩል ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እየገለፅን ቦርዱ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታና በተጨባጭ ያለውን እውነት በጥልቀት በመርመር የወሰነውን ለአንድ ወገን ያደላ ኢ-ፍትሐዊ ውሳኔ በመሻር ከዚህ በፊት በነበሩት 5 አገራዊ ምርጫዎች ሲደረግ በነበረው አግባብ የምርጫ ጣቢያዎቹ እንዲቋቋሙ እያሳሰብን ይህ የማይሆን ከሆነ በአገራዊ ምርጫው ለመሳተፍ የምንቸገር መሆኑን እናሳውቃለን” ሲል የያዘውን አቋም በግልጽ አሳውቋል።

የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ በክልሉ የታየው ሰላምና ኢትዮጵያዊ የአንድነት መንፈስ በውሳኔው ሳቢያ እክል እንዳይገጥመው ስጋት ያደረባቸው ወገኖች ጉዳዩ በጊዜ የተሻለ መፍትሄ ካልተበጀለት ለአጠቃላይ ሀገሪቱ አደጋ ሊሆን እንደሚችል እየተናገሩ ነው።

LEAVE A REPLY