ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከነገ መጋቢት 21 2013 ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት የማህበር ቤት ምዝገባ እንደሚካሄድ አስታወቀ፡፡
ከቀናት በፊት በማህበር ተደራጅተው ቤት ለመገንባት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ነዋሪዎች ምዝገባ እንደሚጀምር ገልፆ የነበረው ቢሮው፣ በ2005 ነባር በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ቁጠባቸውን ያላቋረጡ፣ በማህበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት ፍላጎቱ ያላቸው ተመዝጋቢዎች፣ በማህበር ከተደራጁ በኋላ ከእያንዳንዱ አባል የሚጠበቀውን የቤቱን ወጪ የ70 በመቶ ክፍያ በቅድሚያ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ ተመዝጋቢዎች ወደ ቢሮ በመምጣት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ/Online/ በቢሮው አድራሻ WWW.aahdab.gov.et አማካኝነት ከነገ ማክሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት/ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ/ ምዝገባችውን ማካሄድ እንደሚችሉ ገልጿል፡፡
ነባሩ የ20/80 እና የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ግንባታ ስራ በተለመደው አሰራር እንደሚቀጥልም ቢሮው አያይዞ አመልክቷል።