ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በእነ አቶ አራርሶ ቢቂላ ሰብሳቢነት ባከናወነው ጠቅላላ ጉባኤ አዳዲስ አመራሮችና የምርጫ ተፎካካሪ ዕጩዎች መምረጡን በማስታወቅ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሳታፊነት ጥያቄ አቅርቦ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጥያቄው በቦርድ በኩል ውድቅ መደረጉ ታውቋል።
ቦርዱ ትናንት መጋቢት 19/2013 ባወጣው መግለጫ በጉባኤው የተመረጡትን አዲስ አመራሮች እንደ ኦነግ አመራሮች መቀበል እንደማይችል ገለጿል። ከዚህም በተጨማሪ ምርጫው ውስጥ ለመሳተፍና እጩዎች ለማቅረብ ኦነግ ያቀረበውን ጥያቄ አሁን የተመረጠው አመራር ተቀባይነት ካለማግኘቱ ጋር በተያያዘም ቦርዱ ጥያቄውን ማየት እንዳላስፈለገው አስታውቆ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓል።