ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሥልጣን የያዙበትን 3ኛ ዓመት አስመልክቶ በተሸከርካሪ የታጀበ የድጋፍ ሰልፍ የፊታችን ዓርብ በአዲስ አባበ ሊካሄድላቸው ነው ተብሏል።
ከማኅበረሰቡ የተውጣጡ ግለሰቦች፣ የኃይማኖት አባቶችና ባለሃብቶች የድጋፍ ሰልፉን በማስመልከት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው እንደተመለከተው፣ ዓርብ መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሥልጣን የያዙበትን 3ኛ ዓመት አስመልክቶ በተሽከርካሪ ትርዒት የታጀበ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።