የመቀሌ ጊዜያዊ ከንቲባ ራሳቸውን ከሃላፊነት አገለሉ!

የመቀሌ ጊዜያዊ ከንቲባ ራሳቸውን ከሃላፊነት አገለሉ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናየመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አታኽልቲ ኃይለስላሴ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

አቶ አታኽልቲ ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ ለድረገፁ በሰጡት ቃል ያረጋገጡ ሲሆን፣ ስልጣናቸውን ሊለቁ የቻሉበትን ዝርዝር ምክንያት በቅርቡ እንደሚያሳውቁም አዲስ ስታንዳርድ በድረ ገፁ ጠቁሟል።

የትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳዳሪ የሆኑት ዶክተር ሙሉ ነጋ መስተዳደሩ በግምገማ ላይ መሆኑን ጠቅሰው የሰራ ሃላፊነታቸውን ባግባቡ ያልተወጡ አመራሮችን እየቀነሱ መሆናቸውን መገናኛ ብዙሀን ጠቁመዋል።

LEAVE A REPLY