ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከቀናት በፊት ጋና ላይ ለሚዘጋጀው 33ኛው አፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ላረጋገጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን (ዋልያዎቹ)፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቷል።
ዛሬ በተከናወነው የሽልማት ስነ ሥርዓት ላይ የተገኙት
ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድኑ ላስመዘገበው ውጤት አስተዳደሩ እጅግ የላቀ ክብርና አድናቆት እንዳለው ገልፀው፤ የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም ለብሄራዊ ቡድኑ እና ለአጠቃላይ የስፖርቱ እድገት ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።
አያይዘውም “በጥረታችሁ ታሪክ ለማስመዝገብ በመብቃችሁ ለሃገራችሁ የተለየ የመነቃቃት ስሜት ፈጥራችኋል” ብለዋል።