የጠ/ሚኒስትሩ 3ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከበረ!

የጠ/ሚኒስትሩ 3ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከበረ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በፓርላማ የተመረጡት የዶክተር ዐቢይ አሕመድ 3ኛ ዓመት በዓለ ሲመት፣ በሸራተን አዲስ ተከበረ፡፡

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የተካሄደው ፕሮግራም “ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ወደ ሃላፊነት የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአመራራቸው ያስመዘገቧቸውን ስኬቶች ለመዘከር ያለመ መርሃ ግብር ነው” ተብሏል።

የሶስት አመቱን የለውጥ ጉዞ የሚዳስስ ጥናታዊ ፅሁፍ በቀረበበት በዚሁ መርሃ ግብር፣ ዛሬም የብዙዎች ጥያቄ የሆነው የሰላም ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው የተጠየቀ ሲሆን፣ ያልጎለበተ የዴሞክራሲ ባህል፣ ብሄርና ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች፣ ያልተቋጨው የህዳሴ ግድብ ድርድር፣ የታጠቁ ሃይሎች ያልተገታ እንቅስቃሴ የለውጡ ስጋትና ፈተና ተብለው ተጠቅሰዋል፡፡

LEAVE A REPLY