ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳና ተያያዥ ጉዳዮች ማስፈፀሚያ በመንግሥት 98 ሚሊዮን ብር መመደቡ ተገለጸ። ከተመደበው ውስጥም የተወሰነው መጠን በሚቀጥለው ሳምንት ለፖለቲካ ፓርቲዎች መከፋፈል ይጀምራል ተብሏል።
ለፓርቲዎች የሚሰጠው ገንዘብ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት እንዲከፋፈል በቀመር አማካኝነት የተደለደለ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።