በእነ አቶ ስብሃት ነጋ ላይ ሊሰማ የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ታገደ!

በእነ አቶ ስብሃት ነጋ ላይ ሊሰማ የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ታገደ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዐቃቤ ህግ አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ የ42 ተጠርጣሪዎችን የጊዜ ቀጠሮ እየተመለከተ ላለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ችሎት የምስክርነት ሂደቱ በዝግ ችሎት እና በስውር እንዲሆን ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል።

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ይህንን አቤቱታ ተቃውመው ለችሎት አቅርበው መቃወሚያቸው ውድቅ ተደርጎ ነበር

የተከሳሽ ጠበቆች በምስክር አሰማም ሂደቱ ላይ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለታቸው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በእነ ስብሃት ነጋ ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሊያሰማው የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ዛሬ መጋቢት 29/2013 ዓ.ም ለጊዜው ታግዷል።

LEAVE A REPLY