ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በድሬደዋ ከተማ መካሄድ በጀመረው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ እየታመሱ መሆኑ ተገለፀ።
የክለቦቹ ተጫዋቾች በከፍተኛ ሁኔታ የቫይረሱ ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ያመለከቱ የአገር ውስጥ ስፖርት መረጃ ምንጮች፣ የወላይታ ድቻ – ስምንት ተጫዋቾች፣ የሐዋሳ ከተማ – ሰባት ተጫዋቾች፣ የባህርዳር ከነማ አራት ተጫዋቾች፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ – ሶስት ተጫዋቾች፣ የሲዳማ ቡና ሀያ ሰባት የቡድን አባላቱ እና የአዳማ ከተማ ከአስራ አምስት በላይ ተጫዋቾች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጠው፤ የሰበታ ከተማ ተጫዋቾችም በትላንትናው ዕለት አዲስ ምርመራ አድርገው ውጤት በመጠባባቅ ላይ እንደሆኑ አመልክተዋል።
አዳማ ከተማ እና ሲዳማ ቡና በትላንትናው ዕለት በድሬዳዋ ያደረጉትን የምርመራ ውጤት በመጠራጠራቸወው ዛሬ ወደሀረር በመሄድ በድጋሚ ምርመራ ማድረጋቸውንም የመረጃ ምንጮቹ ገልፀዋል።